ይህ መሬት ላይ እግሩን ዘርግቶ የምትመለከቱት የስዊዘርላንድ ፕሬዚዳንት ነው። አላን ቤርሰት ይባላል። በቅርቡ በኒውዮርክ በተካሄደው የመንግስታቱ ድርጅት 73ኛ ጠቅላላ ጉባዔ ላይ ለመሳተፍ በሄደበት ወቅት ከኒውዮርክ ከተባበሩት መንግስታት ግቢ ወጣ ብሎ በሚገኝ መናፈሻ ለስብሰባው የሚያቀርበውን ፅሁፍ ሲያረቅ ነው።
መሬት ላይ ከመቀመጡ ይልቅ በጋዜጠኞች ዘንድ መነጋገሪያ የነበረው በኒውዮርክ ቆይታው አብረውት ከተጓዙት የስዊዝ ልዑካን አባላት ጋር ተከራይተውት በነበረው አነስተኛ አፓርታማ የራሱን ምግብ እያበሰለ ሲመገብ መቆየቱ ነው። ፕሬዚዳንቱ በኒውዮርክ ቆይታቸው አንድም ጠባቂ ወይም አጃቢ አልነበራቸውም።
No comments:
Post a Comment