ከሰንጋ ተራው ልጅ ደረሰኝ ስሞታ፣
ከግራሯ ዛፍ ስር ከዶሮዎች ቦታ።
እርግጥ ነው አውቃለው ሀሰት የለበትም፣
ያለው ሁሉ እውነት ቅሬታ የለኝም።
የሰንጋ ተራ ልጅ መላ የማያጣው፣
ዶሮዋን ከፈንግል አክሞ የሚያድነው፣
ለካምፑ ልጅ ሙና ሸውዶ የሚሸጠው።
የዚህ ሰው ታሪኩ መች ተነግሮ ያልቃል፣
ሶስቱም ቀበሌ ላይ ትዝታ አስቀምጧል።
አሻሌና መኮ ገምቤልቱና ቀርሳ እንኳንና ህዝቡ አራዊት ያውቁታል።
ከደጉ ፣ወልደየስ፣በቀለ ደበሌ፣
ያኔ ሲያንቆረቁር ጠጁን በብርሌ።
ከሰኞ ፣ማክሰኞ መቲ ቡልጋ ጠላ፣
ፊሊተር ጠጥቶ አንጀት እየበላ።
አኒ ኤኙ ብሎ አይኑን በእጁ ይዞ፣
የጓደኞቹን ስም እያስጠራ አፍዞ።
አክርማና አዱፋ አቆላልፎ አስሮ፣
ሴት ወንዱን ሲደፋ እርሱ በሳቅ ሰክሮ።
አቤት የተንኮሉ የሀይሉ አባገሮ።
አቤት ልጅነቴ
ማርና ወተቴ
ይህንን ጨወታ የሚያስታውስ ማነው፣
ከፍቅር በስተቀር ክፋት የማያውቀው።
አሁንስ ሳስበው የማውቅህ መሰለኝ፣
አንዱ አብሮ አደጌ ፊቴ እየመጣብኝ፣
ሀይልዬ በሞቴ ማነህ ተው ንገረኝ፣
እንደ "ዲምቱ ጉራቲ" አትጫወትብኝ።
እኔና ኮኒዬን ሀሳብ ላይ የጣልከን፣
ይህንን ጭካኔ ማን አስተማረብን።
ከግራሯ ዛፍ ስር ከዶሮዎች ቦታ።
እርግጥ ነው አውቃለው ሀሰት የለበትም፣
ያለው ሁሉ እውነት ቅሬታ የለኝም።
የሰንጋ ተራ ልጅ መላ የማያጣው፣
ዶሮዋን ከፈንግል አክሞ የሚያድነው፣
ለካምፑ ልጅ ሙና ሸውዶ የሚሸጠው።
የዚህ ሰው ታሪኩ መች ተነግሮ ያልቃል፣
ሶስቱም ቀበሌ ላይ ትዝታ አስቀምጧል።
አሻሌና መኮ ገምቤልቱና ቀርሳ እንኳንና ህዝቡ አራዊት ያውቁታል።
ከደጉ ፣ወልደየስ፣በቀለ ደበሌ፣
ያኔ ሲያንቆረቁር ጠጁን በብርሌ።
ከሰኞ ፣ማክሰኞ መቲ ቡልጋ ጠላ፣
ፊሊተር ጠጥቶ አንጀት እየበላ።
አኒ ኤኙ ብሎ አይኑን በእጁ ይዞ፣
የጓደኞቹን ስም እያስጠራ አፍዞ።
አክርማና አዱፋ አቆላልፎ አስሮ፣
ሴት ወንዱን ሲደፋ እርሱ በሳቅ ሰክሮ።
አቤት የተንኮሉ የሀይሉ አባገሮ።
አቤት ልጅነቴ
ማርና ወተቴ
ይህንን ጨወታ የሚያስታውስ ማነው፣
ከፍቅር በስተቀር ክፋት የማያውቀው።
አሁንስ ሳስበው የማውቅህ መሰለኝ፣
አንዱ አብሮ አደጌ ፊቴ እየመጣብኝ፣
ሀይልዬ በሞቴ ማነህ ተው ንገረኝ፣
እንደ "ዲምቱ ጉራቲ" አትጫወትብኝ።
እኔና ኮኒዬን ሀሳብ ላይ የጣልከን፣
ይህንን ጭካኔ ማን አስተማረብን።
No comments:
Post a Comment