Free E. Books coming soon

  • Amharic Books Fiction
  • Amharic Books History
  • Amharic Books Religious
  • Amharic Books Secular

Thursday, November 1, 2018

#ውቃቢዬ_የከሸፈ_ቢሆንም አዲሷን የጠ/ፍቤት ፕሬዚደንት ላስተዋውቃችሁ...
ወ/ሮ መዐዛ አሸናፊ ማን ናቸው ?
በ 1956 በቤኒሻንጉል ጉሙዝ አሶሳ የተወለዱት የህግ ባለሙያዋ ወ/ሮ መዐዛ አሸናፊ ስመጥር የሴቶች መብት አቀንቃኝ ሲሆኑ የኢትዮጵያ የህግ ባለሙያ ሴቶች ማህበር መስራችና ዳይሬክተር ናቸው፡፡
ከአሜሪካው ኬንት ዩኒቨሪስቲ በአለም አቀፍ ግንኙነት ሁለተኛ ዲግሪያቸውን ያገኙ
ሲሆን የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን ከአዲስ አበባ ዩኒቨሪስቲ አግኝተዋል፡፡
ወ/ሮ መዐዛ አሸናፊ ከ1981-1984 የከፍተኛ ፍርድ ቤት ዳኛ ሆነው ሰርተዋል፡፡
በ1985 የኢትዮጵያ ህገመንግስት አርቃቂ ኮሚሽን አባልና የህግ አማካሪ ሆነው ያገለገሉ ሲሆን በ1987 የኢትዮጵያ የህግ ባለሙያ ሴቶች ማህበርን መስርተዋል፡፡
የመጀመሪያውን የሴቶች ባንክ እናት ባንክን ምስረታ አግዘዋል፤ በ2008 የቦርድ ሰብሳቢ ሆነው አገልግለዋል፡፡
በ2003 የሀንገር ፕሮጀክት የአፍሪካ ሴቶች ሽልማት አሸናፊ እና ከሁለት አመት በሁዋላ የኖቬል የሰላም ሽልማት እጩ ነበሩ፡፡
በ2009 ባደረጉት ንግግር የኢትዮጵያ ሴቶችን የሚያንቋሽሹ የአማርኛ ምሳሌያዎ ንግግሮችን ተችተዋል፡፡
ወ/ሮ መዐዛ አሸናፊ ለኢትዮጵያ ሴቶች መብት መከበራ ያለመታከት የሰሩና እየሰሩ ያሉ እንስት ናቸው፡፡

No comments:

Post a Comment