Free E. Books coming soon

  • Amharic Books Fiction
  • Amharic Books History
  • Amharic Books Religious
  • Amharic Books Secular

Thursday, November 1, 2018



By Yegize Welafen
ለአይጡ ሲባል ዳዋው አይመታ!!
************
ጠ/ሚኒስተር ዶ/ር አብይ ‹ለአይጡ ሲባል ዳዋው አይመታ› እንዳሉት አሊያም ደግሞ አንዲት ትኋን ለማጥፋት ሙሉ ቤቱን እንዳቃጠለው ግለሰብ ወደ ትግራይ የሚወስዱ መንገዶች ሁሉ እየተዘጉ ስለመሆናቸው መረጃዎች እየወጡ ነው፡፡ ነገር ግን ማንን ለመጉዳት ይሆን? ወደ ትግራይ የሚወስዱ መንገዶች ሁሉ ቢዘጉ ለወያኔዎች ምናቸው ነው? እነሱ በዘረፉት ገንዘብ 5 ኮከብ ሆቴል ላይ በየዕለቱ ውስኪያቸውን እየተራጩ ለ40 ዓመት በእነሱ ምክንያት ለደቀቀው ለምስኪኑ የትግራይ ህዝብ ጭንቅ እንጂ ትርፍ የለውም፡፡ አዎን! 27 ዓመት ሙሉ የተመቸው ለህወሃት ሠዎችና ደጋፊዎች እንጂ ልጆቻቸውን ለጦርነት ለገበሩ፣ለማገሩ የሚጦራቸው ላጡ የትግራይ እናትና አባቶች መች ሆነ፡፡ ዛሬም ጉምቱ የህወሃት ሠዎች በብልጠት ትግራይ መሸጉ እን ጂ የተመቻቸው የትግራይ ተወላጆች ትግራይ ውስጥ መች ይኖራሉ፡፡ በውጭ ሀገራትና በአዲስ አበባ መኖራቸውን ማረጋገጫ አያስፈልገንም፡፡ ጎስቋላውና ዛሬም ከመከራ ያልተላቀቀው ምስኪኑ የትግራይ ህዝብ ግን በእነዚህ ክፉዎች በየጊዜው የሚደርስበትን ስቃይ ተቋቁሞ ከመኖር በዘለለ በምን ጉዳይ ሲጠቅሙት አየን? የህወሃት ጅቦች ምስኪኑን የትግራይን ህዝብ ዛሬም መሸሸጊያ አድርገውት፣የውሸት ተስፋ እየሰጡት፣እያስፈራሩትና እየተጫኑት ስለመሆናቸው ከምናየው በላይ ምን ማስረጃ ያስፈልጋል፡፡ ከዚህ ቀደምም ብዬዋለሁ፤የትግራይን ህዝብ ከወያኔ መከራና ስቃይ ነፃ የምናወጣው እኛ ነን፡፡ ምክንያቱም ከ80 ፐርሠንቱ በላይ በትግራይ የሚኖሩት የትግራይ ተወላጆች አቅመ ደካሞች፣ዕድሜያቸው የገፋና ህወሃትን ለመቃወም እንኳን ብርታት የሌላቸው ናቸው፡፡ ከዚህ ውጭ ለጥፋት የተዘጋጁ ወታደሮችና በሠሩት ወንጀል እንዳይጠየቁ ሸሽተው የሄዱ እንጂ አሁንም ትግራይ ውስጥ የትግራይ ተወላጆች ይኖራሉ ማለት አይቻልም፡፡ የሆነው ሆኖ ሁሌ በግሽግሽና በዛቻ ከመኖር በተገኘው አጋጣሚ ወያኔን ማኮላሸትና ዳግም ነፍስ እንዳይዘራ ማድረግ እንጂ መንገድ በመዝጋትና የኤሌክትሪክ መብራት በመቁረጥ ይዳከማል ብለን ልናስብ አይገባም፡፡ ሞት ለወያኔ!!

No comments:

Post a Comment