Free E. Books coming soon

  • Amharic Books Fiction
  • Amharic Books History
  • Amharic Books Religious
  • Amharic Books Secular

Thursday, November 1, 2018



By Yegize Welafen
ለአይጡ ሲባል ዳዋው አይመታ!!
************
ጠ/ሚኒስተር ዶ/ር አብይ ‹ለአይጡ ሲባል ዳዋው አይመታ› እንዳሉት አሊያም ደግሞ አንዲት ትኋን ለማጥፋት ሙሉ ቤቱን እንዳቃጠለው ግለሰብ ወደ ትግራይ የሚወስዱ መንገዶች ሁሉ እየተዘጉ ስለመሆናቸው መረጃዎች እየወጡ ነው፡፡ ነገር ግን ማንን ለመጉዳት ይሆን? ወደ ትግራይ የሚወስዱ መንገዶች ሁሉ ቢዘጉ ለወያኔዎች ምናቸው ነው? እነሱ በዘረፉት ገንዘብ 5 ኮከብ ሆቴል ላይ በየዕለቱ ውስኪያቸውን እየተራጩ ለ40 ዓመት በእነሱ ምክንያት ለደቀቀው ለምስኪኑ የትግራይ ህዝብ ጭንቅ እንጂ ትርፍ የለውም፡፡ አዎን! 27 ዓመት ሙሉ የተመቸው ለህወሃት ሠዎችና ደጋፊዎች እንጂ ልጆቻቸውን ለጦርነት ለገበሩ፣ለማገሩ የሚጦራቸው ላጡ የትግራይ እናትና አባቶች መች ሆነ፡፡ ዛሬም ጉምቱ የህወሃት ሠዎች በብልጠት ትግራይ መሸጉ እን ጂ የተመቻቸው የትግራይ ተወላጆች ትግራይ ውስጥ መች ይኖራሉ፡፡ በውጭ ሀገራትና በአዲስ አበባ መኖራቸውን ማረጋገጫ አያስፈልገንም፡፡ ጎስቋላውና ዛሬም ከመከራ ያልተላቀቀው ምስኪኑ የትግራይ ህዝብ ግን በእነዚህ ክፉዎች በየጊዜው የሚደርስበትን ስቃይ ተቋቁሞ ከመኖር በዘለለ በምን ጉዳይ ሲጠቅሙት አየን? የህወሃት ጅቦች ምስኪኑን የትግራይን ህዝብ ዛሬም መሸሸጊያ አድርገውት፣የውሸት ተስፋ እየሰጡት፣እያስፈራሩትና እየተጫኑት ስለመሆናቸው ከምናየው በላይ ምን ማስረጃ ያስፈልጋል፡፡ ከዚህ ቀደምም ብዬዋለሁ፤የትግራይን ህዝብ ከወያኔ መከራና ስቃይ ነፃ የምናወጣው እኛ ነን፡፡ ምክንያቱም ከ80 ፐርሠንቱ በላይ በትግራይ የሚኖሩት የትግራይ ተወላጆች አቅመ ደካሞች፣ዕድሜያቸው የገፋና ህወሃትን ለመቃወም እንኳን ብርታት የሌላቸው ናቸው፡፡ ከዚህ ውጭ ለጥፋት የተዘጋጁ ወታደሮችና በሠሩት ወንጀል እንዳይጠየቁ ሸሽተው የሄዱ እንጂ አሁንም ትግራይ ውስጥ የትግራይ ተወላጆች ይኖራሉ ማለት አይቻልም፡፡ የሆነው ሆኖ ሁሌ በግሽግሽና በዛቻ ከመኖር በተገኘው አጋጣሚ ወያኔን ማኮላሸትና ዳግም ነፍስ እንዳይዘራ ማድረግ እንጂ መንገድ በመዝጋትና የኤሌክትሪክ መብራት በመቁረጥ ይዳከማል ብለን ልናስብ አይገባም፡፡ ሞት ለወያኔ!!


ከሰንጋ ተራው ልጅ ደረሰኝ ስሞታ፣
ከግራሯ ዛፍ ስር ከዶሮዎች ቦታ።
እርግጥ ነው አውቃለው ሀሰት የለበትም፣
ያለው ሁሉ እውነት ቅሬታ የለኝም።
የሰንጋ ተራ ልጅ መላ የማያጣው፣
ዶሮዋን ከፈንግል አክሞ የሚያድነው፣
ለካምፑ ልጅ ሙና ሸውዶ የሚሸጠው።
የዚህ ሰው ታሪኩ መች ተነግሮ ያልቃል፣
ሶስቱም ቀበሌ ላይ ትዝታ አስቀምጧል።
አሻሌና መኮ ገምቤልቱና ቀርሳ እንኳንና ህዝቡ አራዊት ያውቁታል።
ከደጉ ፣ወልደየስ፣በቀለ ደበሌ፣
ያኔ ሲያንቆረቁር ጠጁን በብርሌ።
ከሰኞ ፣ማክሰኞ መቲ ቡልጋ ጠላ፣
ፊሊተር ጠጥቶ አንጀት እየበላ።
አኒ ኤኙ ብሎ አይኑን በእጁ ይዞ፣
የጓደኞቹን ስም እያስጠራ አፍዞ።
አክርማና አዱፋ አቆላልፎ አስሮ፣
ሴት ወንዱን ሲደፋ እርሱ በሳቅ ሰክሮ።
አቤት የተንኮሉ የሀይሉ አባገሮ።
አቤት ልጅነቴ
ማርና ወተቴ
ይህንን ጨወታ የሚያስታውስ ማነው፣
ከፍቅር በስተቀር ክፋት የማያውቀው።
አሁንስ ሳስበው የማውቅህ መሰለኝ፣
አንዱ አብሮ አደጌ ፊቴ እየመጣብኝ፣
ሀይልዬ በሞቴ ማነህ ተው ንገረኝ፣
እንደ "ዲምቱ ጉራቲ" አትጫወትብኝ።
እኔና ኮኒዬን ሀሳብ ላይ የጣልከን፣
ይህንን ጭካኔ ማን አስተማረብን።


ይህ መሬት ላይ እግሩን ዘርግቶ የምትመለከቱት የስዊዘርላንድ ፕሬዚዳንት ነው። አላን ቤርሰት ይባላል። በቅርቡ በኒውዮርክ በተካሄደው የመንግስታቱ ድርጅት 73ኛ ጠቅላላ ጉባዔ ላይ ለመሳተፍ በሄደበት ወቅት ከኒውዮርክ ከተባበሩት መንግስታት ግቢ ወጣ ብሎ በሚገኝ መናፈሻ ለስብሰባው የሚያቀርበውን ፅሁፍ ሲያረቅ ነው።
መሬት ላይ ከመቀመጡ ይልቅ በጋዜጠኞች ዘንድ መነጋገሪያ የነበረው በኒውዮርክ ቆይታው አብረውት ከተጓዙት የስዊዝ ልዑካን አባላት ጋር ተከራይተውት በነበረው አነስተኛ አፓርታማ የራሱን ምግብ እያበሰለ ሲመገብ መቆየቱ ነው። ፕሬዚዳንቱ በኒውዮርክ ቆይታቸው አንድም ጠባቂ ወይም አጃቢ አልነበራቸውም።
ታዲያ ጋዜጠኞች በአለም በኢኮኖሚ ቀደምት ከሆኑት አገሮች አንዷ የሆነችው ስዊዝ ፕሬዚዳንትን ድርጊትና በራስ መተማመን ከአፍሪካ መሪዎች ጋር መማወዳደር የተለያዩ ትችቶችን በመሰንዘር ላይ ናቸው። እንደ ምሳሌም የኡጋንዳው ፕሬዚዳንት ዩዌሪ ሙሴቬኒ ስልክ ለማውራት በመፈለጋቸው እስኪጨርሱ መንገዶች ለትራፊክ ዝግ ከመደረጋቸው ጋር በማነፃፀር ተችተዋል።
የኛዎቹንም ማመሳሰል ግድ ይለናል...




አምባሳደር ሳህለወርቅ ዘውዴ በነገው እለት የመጀመሪያዋ የኢፌዴሪ ሴት ርእሰ ብሔር ሆነው ሊሾሙ እንደሚችሉ አዲስ ስታንዳርድ፣ ቦርከናና በርካታ የበይነ መረብ መረጃዎች ውስጥ አዋቂ ምንጮችን ጠቅሰው ዘገቡ።
በርእሰ ብሔርነት ደረጃ ነገ ሹመታቸው ሲፀድቅ ከንግሥተ ነገሥታት ዘውዲቱ ምኒልክ በመቀጠል ሁለተኛዋ እንስት እንደሚሆኑ ይጠበቃል።
ዘገቡ። አምባሳደሯ አማርኛ እንግሊዝኛና ፈረንሳይኛን አቀላጥፈው መናገር የሚችሉ ሲሆን፤ ሀገራቸውን በአፍሪካ ሀገሮች በአምባሳደርነት፤ በዓለም አቀፍ ደረጃ በተመድ የአንቶኒዮ ጉቴሬዝ የአፍሪካ ወኪል ሆነው Under Secretary ማዕረግ እያገለገሉ ነው።
በሀገራችን ታሪክ እንደ እሌኒ፣ ምንትዋብ፣ ጣይቱ፣ ሎኮ፣ የቃቄ ወርድዎት አይነት ትንታግ እንስቶች የሚታወቁ ሲሆን
በርእሰ ብሔርነት ደረጃ ነገ ሹመታቸው ሲፀድቅ ከንግሥተ ነገሥታት ዘውዲቱ ምኒልክ በመቀጠል ሁለተኛዋ እንስት እንደሚሆኑ ይጠበቃል።


#ውቃቢዬ_የከሸፈ_ቢሆንም አዲሷን የጠ/ፍቤት ፕሬዚደንት ላስተዋውቃችሁ...
ወ/ሮ መዐዛ አሸናፊ ማን ናቸው ?
በ 1956 በቤኒሻንጉል ጉሙዝ አሶሳ የተወለዱት የህግ ባለሙያዋ ወ/ሮ መዐዛ አሸናፊ ስመጥር የሴቶች መብት አቀንቃኝ ሲሆኑ የኢትዮጵያ የህግ ባለሙያ ሴቶች ማህበር መስራችና ዳይሬክተር ናቸው፡፡
ከአሜሪካው ኬንት ዩኒቨሪስቲ በአለም አቀፍ ግንኙነት ሁለተኛ ዲግሪያቸውን ያገኙ
ሲሆን የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን ከአዲስ አበባ ዩኒቨሪስቲ አግኝተዋል፡፡
ወ/ሮ መዐዛ አሸናፊ ከ1981-1984 የከፍተኛ ፍርድ ቤት ዳኛ ሆነው ሰርተዋል፡፡
በ1985 የኢትዮጵያ ህገመንግስት አርቃቂ ኮሚሽን አባልና የህግ አማካሪ ሆነው ያገለገሉ ሲሆን በ1987 የኢትዮጵያ የህግ ባለሙያ ሴቶች ማህበርን መስርተዋል፡፡
የመጀመሪያውን የሴቶች ባንክ እናት ባንክን ምስረታ አግዘዋል፤ በ2008 የቦርድ ሰብሳቢ ሆነው አገልግለዋል፡፡
በ2003 የሀንገር ፕሮጀክት የአፍሪካ ሴቶች ሽልማት አሸናፊ እና ከሁለት አመት በሁዋላ የኖቬል የሰላም ሽልማት እጩ ነበሩ፡፡
በ2009 ባደረጉት ንግግር የኢትዮጵያ ሴቶችን የሚያንቋሽሹ የአማርኛ ምሳሌያዎ ንግግሮችን ተችተዋል፡፡
ወ/ሮ መዐዛ አሸናፊ ለኢትዮጵያ ሴቶች መብት መከበራ ያለመታከት የሰሩና እየሰሩ ያሉ እንስት ናቸው፡፡